የልደት ምስክር ወረቀት ለማግኘት ስለመወለድ ምዝገባ ማድረግ ይኖርብዎታል።
እርስዎና ልጅዎ አስፈላጊ በሆኑት አገልግሎቶች ላይ ለመጠቀም የምስክር ወረቀት ይረዳል:
- ለመንግሥት አገልግሎቶችና ክፍያዎች
- ለትምህርት ቤት
- ለባንክ አካውንት
- ለፓስፖርት
- ለመንጃ ፈቃድና ለግብር ፋይል ቁጥር ማውጣት ይሆናል።
ሲመዘገቡ ወይንም ከዚያ በኋላ የምስክር ወረቀት ማግኘት ይችላሉ። ለምስክር ወረቀቶች ማውጫ ክፍያዎች ይኖሩታል።
በመስመር ላይ ምዝገባ ቅጽ በእንግሊዝኛ ሲሆን ብዙ ደረጃዎች ይኖሩታል:
- ወላጆች ከሚያዩት አንዱ ድረገጽ www.bdm.vic.gov.au/baby (External link) ሲሆን እንዲሁም ከBDM ጋር ለመመዝገብ አካውንት ለማውጣት ድረገጽ.
ምክር! የሞባይል ስልክዎን ሲጀምሩ ለማካተት ማስታወስ ያለብዎ የ ‘+’ ምልክትን እንዲሁም የአገርን ኮድ ማውጫ (+61 ለአውስትራሊያ)። ለምሳሌ +61430000000. - የመጀመሪያ ክፍሉን ቅጽ መሙላት። ስለ ልጅዎ፤ እርስዎና ሌላው ወላጅ በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይጠየቃሉ።
- ከዚያ በኋላ ሁለተኛው ወላጅ በመስመር ላይ ያለን ቅጽ የእነሱን ክፍል እንዲሞሉት በኢሜል እንልካለን።
አስፈላጊ፡ ስለደህንነት የሆነ አሳሳቢ ጉዳይ ካለዎት (ለምሳሌ፡ ከቤተሰብ ሁከት ጋር በተዛመደ)፤ የትውልድ ምዝገባ በጋራ ሆኖ ህጋዊ ቃል መግለጫ (በመስመር ላይ ይቀርባል) ይህም ለምን ሁለቱ ወላጆች ተሳታፊ መሆን እንደማይቻል ጽሁፋዊ መግለጫ ነው።
BDM ሌላውን ወላጅ ማነጋገር ይኖርበታል። በማስፈራራት ወይም ሁከት ፈጠራ ላይ ማስረጃ ካቀረቡ፤ ከርስዎ ጽሁፋዊ ፈቃድ በስተቀር የርስዎን ማንኛውንም ዝርዝር አድራሻ አውጥተን ለሌላው ወላጅ አንሰጥም።
ከዚህ በበለጠ ምክር ወይም እርዳታ ከፈለጉ በስልክ 1300 369 367 መደወል ይኖርብዎታል። - ሁለተኛው ወላጅ እኛ በላክንለት ኢሜል ላይ በመጫን ያላቸውን ዝርዝር መረጃ በመስመር ላይ ይሞላሉ። ይህ ለምዝገባው ያጠናቅቃል።
- አንደኛው ወላጅ የእነሱን ሂደት ድርሻ ሲያጠናቅቁ ለልደት ምስክር ወረቀት ማዘዝ ይችላሉ።
BDM አገልግሎቶች
በቪክቶሪያ ውስጥ ያሉትን የህይወት ድርጊቶች ዝርዝር መረጃ መዝግበናል። እንዲሁም ለነዚህ ድርጊቶች ምስክር ወረቀት እናቀርባለን።
ስለሚከተለው እኛን ማነጋገር
- ለህጻን መወለድና የልደት ምስክር ወረቀት ስለመመዝገብ
- የሞት ምስክር ወረቀቶች
- የጋብቻ ምስክር ወረቀቶች
- ለዝምድና እና የዝምድና ምስክር ወረቀቶች ምዝገባ
- በ Victorian Marriage Registry በኩል ጋብቻ መፈጸም
- ስም ስለመቀየር
- የጾታ ማረጋገጫ
ለበለጠ መረጃ እና ድጋድ
በራስዎ ቋንቋ ምክር
በራስዎ ቋንቋ የBDM’ን ለማነጋገር የትርጉምና አስተርጓሚ አገልግሎት በስልክ/TIS በስልክ 13 14 50 መደወል። ከ Registry of Births, Deaths and Marriages Victoria ጋር በስልክ 1300 369 367 አድርገው እንዲያነጋግርዎ መጠየቅ።
ለእኛ መደወል
በስልክ፡ 1300 369 367 ከጥዋቱ 8am – 2pm ከሰኞ እስከ ዓርብ (ህዝባዊ ነዓላትን አያካትትም)በ BDM ድረገጽ
ለመጎብኘት www.bdm.vic.gov.au እና ጥያቄ ለማቅረብ ‘እኛን ማነጋገር/Contact Us’ የሚለውን መምረጥ።የፍትህ አገልግሎት ማእከላት/Justice Service Centres
በሞላው ቪክቶሪያ ውስጥ ላሉ የ BDM አገልግሎቶች በፍትህ አገልግሎት ማእከላት በኩል ይቀርባል። ለበለጠ ዝርዝር መረጃ በድረገጽ www.justice.vic.gov.au/service-locations (External link) ላይ መጎብኘት.